በጌምድር ማን ናት?
ጎንደር የበፊቱ በጌምድር ክፍለ ሐገር እና የጥንትዋ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነበር። ዛሬ በስሜን ጎንደር ዞን በአማራ ክልል ሲገኝ ከጣና ሃይቅ ሰሜን አንገረብ ወንዝ ላይ ከሰሜን ተራራ ወደ ደቡብ ምእራብ ሰፍሮ ይገኛል። በ12°36′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°28′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው። አጼ ፋሲለደስ ጎንደርን እንደ ዋና ከተማነት ለመጀመሪያ ጊዜ ይጠቀሙ እንጂ ከዚያ በፊት በአካባቢው ሰወች ይኖሩበት እንደነበር ታሪክ አለ። ሆኖም ግን ከተማው በታሪክ የገነነው አጼ ፋሲለደስ በአሁኑ ፋሲል ግቢ ወይም የነገስታት ግቢ ውስጥ የፋሲል ግንብን በ1636 ሲያንጽ ነበር።
በተጨማሪም.....
No comments:
Post a Comment